እስራኤል በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር ስራ እንደምትደግፍ ገለጸች

“መንግስት በትግራይ ክልል እያካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር በተመለከተ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ አለሙ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ገለጻ አድርገውላቸዋል። 

የእስራኤል ፕሬዝዳንት የውጭ ጉዳይ አማካሪ፣ የጠቅላይ ሚንስትር የብሄራዊ ደህንነት የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ እና መከላከያ ሚንስትር የስራ ሀላፊዎች ጉዳዩን በተመለከተ ኢምባሲው ገለጻ አድርጎላቸዋል። 

በዚህም የእስራኤል ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎቹ የኢትዮጵያ መንግስትን አቋም እንደሚገነዘቡ እና እንደሚደግፉ መናገራቸውን አምባሳደር ረታ አለሙ ተናግረዋል። 

በሀገሪቱ ያሉ ሚዲያዎች የሚያወጧቸውን መረጃዎችን በመቃኘት ትክክለኛ መረጃ የሚደርስበትን ስራ መሰራቱንም በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ አለሙ ተናግረዋል።”

በአስማማው አየነው

:EBC

Leave a Reply